ሊፖሱሽን በዘመናዊ መሳሪያዎች አማካኝነት ስብን ከሰውነት በመምጠጥ እንደ ሆድ፣ ጀርባ፣ መቀመጫ ወዘተ የመሳሰሉ የአካል ክፍሎችን ውብ ቅርፅ የማስያዝ ዘዴ ነው። Liposuction በዋነኝነት የሚመረጠው በራሳቸው ሰብን ማሰወገድ በማይችሉና ውፍረት ለመቀነስ በተለያየ ምክኒያት በሚቸገሩ ነው፡፡ የሊፖሰሽን አገልግሎት በአጠቃላይ በሆስፒታል ውስጥ የአንድ ሌሊት ቆይታ አይፈልግም ፡፡ ህክምና በተፈገው የሰውነት አካል ብቻ ማደንዘዣ በመጠቀም ወይም በአጠቃላይ ማደንዘዣ ሊከናወን ይችላል፡፡ ቀዶ ጥገናው እንደታለመላቸው የሰውነት ክፍሎች ከ1
እሰከ 3 ሰአታት ይወስዳል፡፡ ከቀዶ ጥገናው በኋላ ታካሚው ኮርሴትን ለብሶ መድሃኒቶችን መውሰድ እና የዶክተሮች ምክርን ማክበር የሚያሰፈልግ ሲሆን ወደ ነባር ዕለታዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ ከ7-10
ቀናት ብቻ በቂ ነው፡፡