የስኳር በሽታ በደምዎ ውስጥ ያለው የግሉኮስ (የደም ስኳር) መጠን በጣም ከፍተኛ ከሆነ የሚከሰት በሽታ ነው፡፡ በደምዎ ውስጥ ያለው የግሉኮስ መጠን መጨመር ብዙ የጤና እክሎችን ያስከትላል፡
- የልብ ህመም
- ስትሮክ
- የኩላሊት በሽታ
- የአይን ችግር
- የጥርስ ሕመም
- የነርቭ መጎዳት
- የእግር ችግሮች ወዘተ፡፡
የተለያዩ የስኳር በሽታ ዓይነቶች አሉ፡-
አይነት 1
የስኳር በሽታ፡- ይህ ዓይነት ሊታከም አይችልም ነገር ግን በሚከተለው አመጋገብ እና መድሃኒቶችን በመጠቀም ማስታመም ይቻላል፡፡
አይነት 2
የስኳር በሽታ፡- ይህ አይነት የስኳር በሽታ በብዛት በመካከለኛ እና በእድሜ በገፉት ሰዎች ላይ ይከሰታል። ዓይነት
2 በጣም የተለመደ የስኳር በሽታ ሲሆን በሜታቦሊክ ቀዶ ጥገና ሊድን ይችላል። እንደ ጌስቴሽናል እና ሞኖጅኒክ የስኳር በሽታ ያሉ ሌሎች የስኳር በሽታ ዓይነቶች አሉ ነገርግን ከላይ ከተጠቀሱት ዓይነቶች ያነሱ ናቸው።