የፀጉር ንቅለ ተከላ

የፀጉር መመለጥና መሳሳትን እሰከመጨረሻው ለማሰወገድ ተመራጩ ዘዴ የፀጉር ንቅለ ተከላ ነው፡፡

የጸጉር ንቅለ ተከላ ደረጃዎች፡-

1-    የፀጉር ምርመራ

2-    የፊት የፀጉር መስመር ሥዕል

3-    የፀጉር መላጨት

4-    ማደንዘዣ ማድረግ

5-    ፀጉር ካለበት ክፍል ፎሊክስ ማውጣት

6-    ፀጉር የሚረከልበትን ቀዳዳ መከፈት

7-    ፎሌክስን መትከል

8-    ከቀዶ ጥገናው በነጋታው ፀጉርን መታጠብ

   የፀጉር ንቅለ ተከላ ስራዎች አብዛኛውን ጊዜ ከ6-8 ሰአታት የሚፈጅ ሲሆን ፀጉር የሚወሰድበት እና የመቀበያ ቦታው የማገገሚያ ጊዜ ሁለት ቀን ሲሆን ግለሰቡ በዚህ ወቅት የዶክተሩን መመሪያ መከተል አለበት፡፡ የፀጉር ቀዶ ጥገና የመጨረሻ ውጤት በ 8 ኛው እና በ 12 ኛው ወራት መካከል ይታያል፡፡ ይህ የፀጉር ሥራ ስኬታማነትን ለመገምገም በጣም ጥሩው ጊዜ ነው ፡፡ ለተተከለው ፀጉር ተጨማሪ ልዩ እንክብካቤ አያስፈልግም፡፡ በቀላሉ ሊቆረጥ፣ ሊታጠብ፣ ሊቀረጽ፣ ሊቀባ ወዘተ ይችላል፡፡