የስኳር በሽታ

የስኳር በሽታ በደምዎ ውስጥ ያለው የግሉኮስ (የደም ስኳር) መጠን በጣም ከፍተኛ ከሆነ የሚከሰት በሽታ ነው፡፡ በደምዎ ውስጥ ያለው የግሉኮስ መጠን መጨመር ብዙ የጤና እክሎችን ያስከትላል፡

- የልብ ህመም

- ስትሮክ

- የኩላሊት በሽታ

- የአይን ችግር

- የጥርስ ሕመም

- የነርቭ መጎዳት

- የእግር ችግሮች ወዘተ፡፡

የተለያዩ የስኳር በሽታ ዓይነቶች አሉ፡-

አይነት 1 የስኳር በሽታ፡- ይህ ዓይነት ሊታከም አይችልም ነገር ግን በሚከተለው አመጋገብ እና መድሃኒቶችን በመጠቀም ማስታመም ይቻላል፡፡

አይነት 2 የስኳር በሽታ፡- ይህ አይነት የስኳር በሽታ በብዛት በመካከለኛ እና በእድሜ በገፉት ሰዎች ላይ ይከሰታል። ዓይነት 2 በጣም የተለመደ የስኳር በሽታ ሲሆን በሜታቦሊክ ቀዶ ጥገና ሊድን ይችላል። እንደ ጌስቴሽናል እና ሞኖጅኒክ የስኳር በሽታ ያሉ ሌሎች የስኳር በሽታ ዓይነቶች አሉ ነገርግን ከላይ ከተጠቀሱት ዓይነቶች ያነሱ ናቸው።