የጡት ቅርፅ ማሰተካከያ ቀዶ ጥገና- በእርግዝና፣ ጡት በማጥባት፣ የሰውነት ክብደት መጨመር ወይም መቀነስ፣ እና እርጅና ምክንያት ጡቶች ሊለወጡ፣ ሊረግቡ፣ ቅርፅ ሊያጡ፣ ሊያድጉ ወይም ሊቀነሱ ይችላሉ። እነዚህ ለውጦች እና ቅርፆች በሴቶች አካል እና በስነ-ልቦና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ፡፡ እንደ፡-
• የጡት መጨመር
• የጡት መቀነስ
• የጡት መርገብ
• የጡት አለመመጣጠንን የመሳሰሉ ብዙ አይነት የውበት ቀዶ ጥገናዎች አሉ።
የጡት መጨመር፡ በአጠቃላይ በተለያዩ ምክንያቶች ሙሉ በሙሉ ያላደገች ወይም ጡት በማጥባት አልያም ክብደት ከቀነሰ በኋላ መጠነሱ ባነስ ትንሽ ጡት ላይ ይተገበራል።
የጡት ቅነሳ፡ ትልልቅ ጡቶች ለውበት እና ተግባራዊ ችግሮች፣ እንደ ትከሻ እና ጀርባ ህመም ሊዳርጉ ይችላሉ፡ ጡትን መቀነስ ሁለት አይነት ቴክኒኮች አሉት፡
1) ነፃ የጡት ጫፍ ቴክኒክ
2) የፍላፕ ቴክኒክ ፡፡ የጡት ማንሳት ቀዶ ጥገናዎች አብዛኛውን ጊዜ የሚደረጉት የህመም ስሜትን እና ልቅነትን ለማስተካከል ነው።
የጡት ማንሳት ስራዎች በሚሰሩበት ጊዜ የጡት ቲሹ በህይወት እንዲቆይ ወደሚፈለገው ቦታ ይንቀሳቀሳል፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ በጡቱ ዙሪያ ያሉት ቲሹዎች ይለወጣሉ፡፡ከዛም ጡቱ ተስማሚ ቅርፅ ይሰጠዋል፡፡ የጡት አለመመጣጠን፡ ከእርግዝና፣ ከጡት ማጥባት፣ ከእርጅና፣ ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት መጨመር፣ ከመጠን ያለፈ ክብደት መቀነስ እና የጉርምስና ዕድሜ ወዘተ ጡት ከሌላው የተለየ መጠን ወይም ቅርፅ ሊኖረው ይችላል።